የጁንታው አባላት ከሃገር ለመውጣት ያደረጉት ጥረት በመከላከያ ሰራዊት ከሽፏል - ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ

2 Просмотры
Издатель
ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ፥ ከሃገር ለመውጣት ከሞከሩት የጁንታው አባላት መካከል አብዛኛዎቹ መደምሰሳቸውን እና የተወሰኑት ወደኋላ ተመልሰው ሸለቆ ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ከሃገር ለመውጣትም መታወቂያ በማዘጋጀትና ስማቸውን በሌላ ማንነት በመቀየር በሱዳንና በአማራ ክልል አቋርጠው ለመውጣት መሞከራቸውንም ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጅ ይህ ሙከራና እቅዳቸው ከሽፎ መደምሰሳቸውን ተናግረዋል፡፡
ቀሪዎቹም መውጫ ቀዳዳ ስለሌላቸው መከላከያ ሰራዊት እየተከታተለ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላልም ነው ያሉት፡፡
በመግለጫቸው በትግራይ ክልል ሄሊኮፕተር ተመቷል ተብሎ በጁንታው አባላት የሚናፈሰው አሉባልታ የተለመደ የሃሰት ወሬ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ሌተናል ጀኔራል ባጫ በአጣየ እና አንዳንድ አካባቢዎች ጥቃት ለተፈጸመባቸው ወገኖች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው ለመላው ህዝብም መጽናናትን ተመኝተዋል
Категория
Зарубежные мелодрамы
Комментариев нет.